AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀስላሴ የተገኙበት የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ኮንፈረንስ 2025 በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉባኤው የአየር ንብረት ተለዋዋጭነትን በመቋቋም የተሻሻለ የኑሮ ዘይቤ እና የመስኖ ልማትን ለማጎልበትና ዓለማቀፋዊ ልምድና ተሞክሮዎችን ለመቀመር ያስችላል ተብሏል፡፡
ጉባኤው በተጨማሪም ጠንካራ የመስኖ ስርዓቶችን መተግበር ላይ ማዕከል ያደረገ መሆኑ ተነግሯል።
ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊና ለም መሬት በመስኖ በማልማት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረገጋጥ የምታደርገውን ሰፊ ርብርብ የሚያግዝ ይሆናልም ተብሏል።
የውሃ ሃብት፣ ለመስኖ ልማት የሚውል ምቹና ሰፊ መሬት፣ የማዕድናትና ሌሎችም ፀጋዎች በስፋት ለማልማት ሰፊ ስራዎችን እየሰራች የምትገኘው ኢትዮጵያ በሌማት ቱሩፋት ፣ በበጋ የስንዴ መስኖ ልማት እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስራዎች ስኬታማ መሆን ችላለች።
በጉባኤው ላይ ሚንስትሮች ፣ የተለያዩ ዓለም ሀገራት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ ደጋፊ አካላትና የልማት ድርጅቶች እየተሳተፉበት ይገኛል።
በአሸናፊ በላይ