የሩሲያና ዩክሬይን ጦርነት በሚያበቃበት ሁኔታ ላይ ድርድር እንደሚጀመር ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ

You are currently viewing የሩሲያና ዩክሬይን ጦርነት በሚያበቃበት ሁኔታ ላይ ድርድር እንደሚጀመር ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ

AMN-የካቲት 5/2017 ዓ ም

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ድርድሩ በሚጀመርበት እና ጦርነቱ በሚቋጭበት ሁኔታ ላይ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚን ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ኘሬዝደንት ፑቲንም ሆኑ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ጦርነቱ እንዲቆም ይፈልጋሉ ብለዋል።

ከኘሬዝደንት ፑቲን ጋር ስላደረጉት መልካም ውይይት ለፕሬዝደንት ዘለንስኪ እንደሚገልጹላቸውም ትራምፕ ገልጸዋል ።

የሩሲያና ዪክሬን ድርድር በቅርቡ እንደሚጀምር ገልጸው ድርድሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው እንደሚመሩትም አመልክተዋል ።

ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ላይ ደርሰው ውድመት እያስከተለ የሚገኘው ጦርነት እንደሚያበቃም ተስፋቸውን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review