AMN – የካቲት- 6/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ አለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል የግብርና እና የቆዳ ምርቶች፣የተለያዩ ማዕድናት፣ባህላዊ አልባሳት፣የማኑፋክቸሪንግ እና መሰል ኢኮኖሚያዊያ ፋይዳ ያላቸው ምርቶች የሚቀርቡበት የንግድ ኢግዚቢሽንና ባዛር ዐውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡
በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል የንግድ ኢግዚቢሽን እና ባዛሩ ዐውደ ርዕይ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ሚኒስትሮች፣የአለምአቀፉ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
በዚህም የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ አማራጮችን ለመፍጠር እንዲሁም የቴክኖሎጂ የዕውቀት ሽግግርን ለማሳደግ እንደሚያስችልም ተገልጿል ።
በአዲስ አለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል የሚካሄደው የንግድ ኢግዚቢሽንና ባዛር ዐውደ ርዕይ ከየካቲት 5ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡