ቻይና የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ፑቲን መካከል የሚደረገውን ስብሰባ ለማስተናገድ ዕቅድ እንዳላት ገለጸች

You are currently viewing ቻይና የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ፑቲን መካከል የሚደረገውን ስብሰባ ለማስተናገድ ዕቅድ እንዳላት ገለጸች

AMN – የካቲት 6/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በማለም የሚያደርጉትን ስብሰባ ለማሰናዳት ማቀዷን ቻይና አስታውቃለች፡፡

የቻይና ባለሥልጣናት ለትራምፕ ቡድን በሁለቱ መሪዎች መካከል ስብሰባ እንዲደረግ ለማሸማገል እና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰም ሰላሙን ለማስጠበቅ ጥረት እንደሚያደርጉ ሀሳብ ማቅረባቸው ተመላክቷል፡፡

ትራምፕ በበኩላቸው፣ በትናንትናው ዕለት ከፕሬዚዳንት ፑቲን እና ከፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ጋር ባደረጉት የተናጠል የስልክ ውይይት ሁለቱም ወገኖች ሰላም ለማስፈን ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ውይይት እንዲጀምሩ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተመላክቷል፡፡

ክሬምሊን በበኩሉ፣ ትራምፕ እና ፑቲን ለመገናኘት ከስምምነት እንደደረሱ የገለጸ ሲሆን፣ ፑቲን ትራምፕ ሞስኮን እንዲጎበኙ መጋበዛቸውንም ጠቁሟል፡፡

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሁለቱ መሪዎች የመጀመሪያ ግንኙነት በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ሊካሄድ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉ ጂያኩን፣ ሩሲያ እና አሜሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራት እንደመሆናቸው በወሳኝ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን ቢያጠናክሩ ቻይና ደስታዋ ነው ብለዋል፡፡

ከግጭቱ የመጀመሪያ ወራት ወዲህ ጦርነቱን ለማርገብ ምንም ዓይነት የሰላም ውይይት አልተካሄደም ያሉት ቃል አቀባዩ፣ አሁን ወደ ሦስተኛው ዓመት እየተቃረበ መሆኑን ተናግረዋል።

ቻይና ችግሩን ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ውይይት እና ውይይት እንደሆነ እምነቷ የፀና መሆኑን በመግለጽ፣ ውይይትን ለማስፋት አጥብቃ ስትሞግት መቆየቷን መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review