ኢትዮጵያ ለመበልፀግ ወስናለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለመበልፀግ ወስናለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 8/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ መልክ ለመበልጸግ ወስናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ”የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በነቃ ዴሞክራሲ፣ በተረጋጋ የምጣኔ ሀብት እድገት፣ በዳበረ ባህላዊ ቅርስ፣ ማህበራዊ መሻሻል እና አካባቢን መልሶ በማልማት ኢትዮጵያ ለመበልፀግ ወስናለች ብለዋል፡፡

ይህንን ግብ እውን ለማድረግም “መደመር” የተሰኘ የሽግግር መርህ ላይ የተመሰረተ ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ወደ ሥራ ገብታለች ብለዋል፡፡

“መደመር” የሚለው ቃል የአማርኛ ቃል ሲሆን፣ በቀላሉ ሲነርጂ ተብሎ ወደ እንግሊዝኛ ሊተረጎም የሚችል ፍልስፍና እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

መደመር፣ ብልፅግና፣ ነፃነት፣ አንድነት፣ ደህንነት እና ብሔራዊ ክብርን ለማስጠበቅ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ሀገር በቀል ርዕዮተ ዓለም እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

መደመር የተሰኘው ፅንሰ ሀሳብ በመሠረታዊነት ማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ እድገትን የሚያበረታታ፣ ብዝሃነትን የሚያከብር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ምድር ላሉ የማህበረሰብ መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች ዕድገትን የሚያበረታታ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review