የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማትና የቅርስ ዕድሳት ሥራ የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ ነው፡- ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

You are currently viewing የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማትና የቅርስ ዕድሳት ሥራ የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ ነው፡- ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት እና የቅርስ ዕድሳት ሥራዎች የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ እንደሆኑ የሠላም ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትር ዴዔታው በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነውን የከተማውን የፒያሳ አካባቢ የኮሪደር ልማት፣ የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስትን የቅርስ ጥገናና እድሳት ሥራ ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ የከተሞች ታሪክ ውስጥ ጎንደር ከተማ ጉልህ የኪነ ጥበብ፣ የኪነ ሕንጻና የሥነ መንግስት ታሪክ አላት።

የታሪካዊ ቅርሶች ዕድሳትና ጥገና ሥራ ትውልዱ የነገን ብሩህ ተስፋ አሻግሮ እንዲያይና ተስፋውንም ጠብቆ ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፍ ምቹ የታሪክ ዐውድ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ጎንደር የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት፣ የአብሮነትና የፍቅር እምቅ ፀጋዎች ባለቤትና ሙዚየም መሆንዋን አውስተው፤ የቀደመ ታሪኳን የሚመጥን የልማት ዕድል እንድታገኝ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በጎንደር እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማትና የቅርስ ዕድሳት ሥራ የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሠላምና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በሀገራችን ዘላቂ ሠላም እየተገነባ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ህዝቡ የሠላሙና የልማቱ ባለቤት ራሱ መሆኑን ተገንዝቦ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review