AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተሯ አሁና ኤዚያኮንዋ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በጀመርነው የመልሶ ማልማት ስራ ተደንቀዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
በተለይም በከተማዉ ልማት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ አካታች የልማት እስትራቴጂ መተግበራችንን የልማት ተነሺዎችን መኖሪ ቤት በመጐብኘት ማመልከታቸው እና ከተነሺዎቹ አንደበት መስማታቸዉም እዳስደሰታቸዉ መናገራቸውንም አክለዋል፡፡
እንዲሁም ይህ ለመላው አፍሪካ ከተሞች እንደ ልምድ ሊስፋፋ እና አዲስ አበባም ይህን ሚናዋን ልትወጣ እንደሚገባ መናገራቸውን አመላክተዋል።
በቀጣይም በከተማዋ በሚሰሩ የልማት እና ሰው ተኮር ስራዎች ላይ በጋራ በትብብር እንደምንሰራ በውይይታችን ወቅት ተግባብተናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።