ኢትዮጵያ በአገር ውስጥም ሆነ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት ተመድ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በአገር ውስጥም ሆነ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት ተመድ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከ.ተ.መ.ድ. የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ለረዳት ዋና ፀሐፊዋ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አደርገውላቸዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን ሀገራዊ ምክክር ሒደት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ የኢትዮጵያ ሕዝብም በቅርብ እየተከታተለው እና እየደገፈው መሆኑ አንስተዋል።

ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሚኒስትሩ በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ምንጊዜም ድጋፏን እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸው በእጅጉ እየተሻሻለ መምጣቱን በመግለጽ ቀጣናዊ ችግሮች በውይይት ብቻ ሊፈቱ እንደሚችሉ አንስተዋል።

የተ.መ.ድ. የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአገር ውስጥም ሆነ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት ተመድ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተያያዘ ዶ/ር ጌዲዮን ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር ጋር በአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸው በእጅጉ እየተሻሻለ እንደመጣ ገልጸዋል።ሱዳንን በተመለከተም ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ለሚደረግ ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ልዩ መልዕክተኛዋ ሕብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጣናው እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር መሥራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review