የጂማ ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ተፈራረመ

You are currently viewing የጂማ ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ተፈራረመ

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

በጂማ ከተማ በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣የጂማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የጂማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር ባስተላለፉት መልእክት በጂማ ከተማ የመጀመሪያ ምእራፍ የኮሪደር ልማት በተጠናቀቀበት ማግስት የ5ጂ ኔትወርክ ተጠቃሚ መሆን ችለናል ብለዋል፡፡

ጂማን የበለጠ የሚያስፈነጥረውን የጅማ ስማርት ሲቲ ስናስጀምር የላቀ ደስታ ተሰምቶናልም ብለዋል ከንቲባው ።

ከተማዋን ስማርት ሲቲ ማድረጉ የመደመር እሳቤን መሰረት ያደረገ እና እንደ ሀገር የተያዘዉን ርዕይ ከግብ ለማድረስ የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው የምንኖርበትን ከተማ ለመኖር ምቹ ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም አበክሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ስማርት ሲቲ ለሁለንተናዊ ልማት እና አገልግሎት የላቀ ድርሻ እንዳለው የጠቆሙት ስራ አስፈጻሚዋ አንድን ከተማ ውጤታማ ከማድረግ አኳያም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው ብለዋል።

ስማርት ጅማ ፡ ከተማዋን የሚያዘምን እና አገልግሎትንም የሚያሳልጥ ነው ብለዋል።

አክለውም መሰል ተግባራት በመላው ሃገሪቱ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በትላንተናው እለት በጅማ ከተማ በይፋ የተጀመረው የ5ጂ (5ኛው ትውልድ) ኔትዎርክ አገልግሎት ለጅማ ከተማ የስማርት ሲቲ ግንባታ ትልቅ ሚና አለውም ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review