ለረጅም ዘመናት ብክለትን በማስከተል የጤና ጠንቅ የነበሩ የከተማዋን ወንዞች የማጽዳት እና የማልማት ስራ እየተከናወነ ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ለረጅም ዘመናት ብክለትን በማስከተል የጤና ጠንቅ የነበሩ የከተማዋን ወንዞች የማጽዳት እና የማልማት ስራ እየተከናወነ ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 12/2017 ዓ.ም

ለረጅም ዘመናት ብክለትን በማስከተል የጤና ጠንቅ የነበሩ የከተማዋን ወንዞች የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የከተማ አስተዳደሩን ያለፉት 6 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች 23 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝና ወንዝ ዳርቻን የማጽዳትና የመንከባከብ ስራ መሰራቱን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ስራ በተጨማሪ ፍሳሽን ወደ ወንዞች በመልቀቅ ብክለት ማስከተልን የሚከላከል ደንብ ፀድቆ በመተግበር ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የደረቅ ቆሻሻ አስተዳዳር ስርዓቱን ለማዘመንና የቤት ለቤት ቆሻሻ የመሰብሰብ አገልግሎት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የደረቅ ቆሻሻ የማጓጓዝ አቅምን በማሳደግ እና የቅብብሎሽ ጣቢያዎችን ቀልጣፋ በማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱን በማጠናከር የከተማዋን ፅዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻሻል መቻሉን አብራተዋል፡፡

የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ከማስፋፋት አንፃር በግማሽ ዓመቱ 163.134 (100% በላይ) ሄክታር አዳዲስ የመንገድ ፓርክ እና ቁርጥራጭ ቦታዎችን ማልማትና መንከባከብ ስራ መከናወኑን ያስታወቁት ከንቲባ አዳነች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከእቅድ በላይ 26 ሚሊየን 720 ሺህ 918 ሚሊየን ችግኞችን መትከል መቻሉን አውስተዋል፡፡

አፈፃፀሙም ከባለፈዉ በጀት ዓመት ከተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኞች ወይም የ52 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የከተማዋ የአረንጓዴ ሽፋን በ2010 ዓም ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 20 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review