AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቅቋል።
ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጸጸም ሪፖርት አዳምጦ ከተወያየ በኋላ አጽድቋል።
በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
በመጨረሻም የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሹመትን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቅቋል፡፡