በአንካራ ስምምነት ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

You are currently viewing በአንካራ ስምምነት ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል በተደረሰው የአንካራ ስምምነት ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የመጀመሪያው ዙር ውይይት በቱርኪዬ አንካራ ዛሬ ተካሂዷል።

የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን መድረኩን ባመቻቹት በዚህ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና በሶማሊያ በኩል ደግሞ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ሞሐመድ ኦማር ተካፍለዋል።

ሁለቱም ተወያዮች ስምምነቱን በተጨባጭ ወደ መሬት ለማውረድ እንዲሁም የጋራ ጥቅምን ለማሳካት እየተሠራ እንደሆነ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ቱርኪዬ ሁለቱ ሀገራት ተቀራርበው በጋራ ጉዳዮቻቸው እንዲመክሩ ለምታደርገው ጥረት ምሥጋና አቅርበዋል።

ባለፈው ታህሳስ መጀመሪያ ላይ በቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋባዥነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሐመድ በአንካራ ተገናኝተው ስምምነቱን መፈረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመረጃው አስታውሷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review