የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ረገድ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ረገድ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለቢሮ ሰራተኞች ያዘጋጀውን የደንብ ልብስ ምርቃት መርሀ-ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ፣ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን በቀለ፣ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ፣ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የማዕከሉ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች፣ ኦፊሰሮች አንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ ቢሮው የተሰጠውን ተልዕኮ ከማከናወን ጎን ለጎን የሪፎርም እና የለውጥ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የዚሁ ሁለንተናዊ ሪፎርም አካል የሆነው ለቢሮ ሰራተኞች የተዘጋጀውን የደንብ ልብስ የማስተዋወቅ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን በቀለ፣ አዲስ አበባ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሪፎርም ስራ በማስፋት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በማከናወን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ እንድትሆን ጠንክሮ በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው እና በመመረቃቸው ከተማዋን ውብ እና ድንቅ ከተማ ማድረግ እንደተቻለ፣ የአገልግሎት አሰጣጡንም በዚያ ደረጃ ማሻሻል እና አገልግሎትን በስታንዳርድ ልክ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ በበኩላቸው፣ ተቋሙ የተሰጠዉን ተልዕኮ ለመወጣትና ለስራዎች መሳካት የአመራሩና የሰራተኛው ቅንጅት እና ግንኙነት በቀጣይም አጠናክሮ በማስቀጠል የስራ አፈጻጸሙን ከዚህ የተሻለ በማድረግ ውጤታማነቱን ማረጋገጥ ይችላል ብለዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review