AMN-የካቲት 13/2017 ዓ.ም
ባሳለፍነው ሰኞ ከአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ተነስቶ ካንዳ ቶሮንቶ ሲጓዝ የነበረ የዴልታ አየርመንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን የመገልበጥ አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ይታወሳል፡፡
አየር መንገዱ በአደጋው ወቀት አውሮፕላን ውስጥ ለነበሩ መንገደኞች ለእያንዳንዳቸው 30 ሺ ዶላር ሊከፍል መወሰኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
76 ተሳፋሪዎች እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረው ይህ አውሮፕላን አደጋ ከደረሰበት በኋላ ወደ አካባቢው ሆስፒታሎች ከተወሰዱ 21 መንገደኞች ውስጥ 19ኙ ህክምና አግኝተው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተነግሯል፡፡የተቀሩት ደግሞ ከባድ ጉዳት እንዳተናገዱ ተዘግቧል፡፡
የአደጋው መንስዔ በምርመራ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በቶለሳ መብራቴ