19 ቁጥር እና ሴኔጋላውያን ፤

You are currently viewing 19 ቁጥር እና ሴኔጋላውያን ፤

AMN-የካቲት 11 ቀን 2017 አ.ም

በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ሶስት ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ አንድ ጊዜ ዋንጫ ማንሳት ችላለች ሴነጋል፤

በተለይ ወርቃማ ስብስብ የተባለለት የ2002ቱ የቴራንጋ አንበሶች በማሊው አፍሪካ ዋንጫ በድንቅ ብቃት ታጅቦ ለፍጻሜ የደረሰ ሲሆን በካሜሮን ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ የሚታወስ ነው፤

ያምሆኖ ሴኔጋል በደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጣምራ አዘጋጅነት በተካሄደው የ2002ቱ አለም ዋንጫ ከመሳተፍ ባለፈ እስካሁን የሚዘከርላት ታሪክ አጽፋለች፤

የወቅቱ የአለም ሻምፒዮኗ ፈረንሳይ እና ቅኝ ተገዢዋ ሴኔጋል በምድብ በአንድ ላይ ነበር የተደለደሉት፤

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም መክፈቻው በተካሄደበት በሴኡል አለም አቀፍ ስታዲየም ተደረገ፤

የግምት ሚዛኑ ለአለም ሻምፒዮኗ ፈረንሳይ ያደላ ነበር፤ የፊፋ ዶትኮም መረጃ እንዳስነበበው በታሪክ ውስጥ አንዳንድ ሁነቶች እና ክስተቶች አይረሴ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ፤ከእነዚህም ፈረንሳይ በሴኔጋል 1ለ0 የተሸነፈችበት የአለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ይጠቀሳል፤

ትዝታውን የበለጠ አይረሴ የሚያደርገው ደግሞ 19 ቁጥር ለባሹ አማካኝ ተከላካይ ፓፓ ቦኡፓ ዲዮፕ ወሳኟን እና ማሸነፊያዋን ጎል ካስቆጠረ በሁዋላ ደስታውን የገለጸበት መንገድ የተለየ ስለመሆኑ አክሏል፡፡

እኔን ጨምሮ ብዙ ሴኔጋላውያን የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊ ነበርን ፤በ1998ቱ አለም ዋንጫ ሀገሪቱ ያዘጋጀችውን የአለም ዋንጫ ብራዚልን አሸንፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ሰትሆን አደባባይ ወጥተን ደስታችንን ገልጸናል፤ከአራት አመታት በሁዋለ ደግሞ ከምንደግፈው ቡደን ጋር ተገናኝተን አሸነፍናት፤አጋጣሚው በእኔ ፤በቤተሰቦቼ እና በመላው ሴኔጋለውያን ዘንድ የተለየ ቦታ የሚሰጠው ነው ሲል ዲዮፕ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ታድያ ተጨዋቹ በብሄራዊ ቡድን ውስጥ 19 ቁጥር ለብሶ ፈረንሳይን ድል በማድረጋቸው አሁንም ድረስ በሴኔጋላውያን ዘንድ ቁጥሩ እንደ ገድ መታየቱን ቀጥሏል ሲል ዘገባው ጥንክሩን አጠቃሏል ፡፡

በበላይነህ ይልማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review