አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርትን ይፋ ተደረገ

You are currently viewing አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርትን ይፋ ተደረገ

AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርትን ይፋ አደረገ ፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ኢትዮጽያ በአይነቱ በይዘቱ እና ዘመኑን በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀ ፓስፖርት እዉን አድርጋለች ብለዋል፡፡

ፓስፖርቱ የዜጎችን ክብር ከሀገራቸዉ መለያ እና ቅርሶች ጋር አካቶ የያዘ ነዉ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ፡፡

ዘመኑን የሚመጥን ሆኖ የተዘጋጀዉ ይህ ፓስፖርት የተሳለጠ ግልጋሎትን ለመለገስ እና በአለም ተወዳዳሪ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ፓስፖርት የዜጎች ማንነት መለያ የሀገር ክብር መለኪያ ነዉ ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ እዉን የሆነዉ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት የዜጎችን ክብር የሚያስጠብቅ የኢትዮጵያን ልክ የሚመጥን ነዉ ብለዋል፡፡

አዲሱ ፓስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀ እና በሀገር ዉስጥ የሚመረት ነዉ ተብሏል፡፡

ፓስፖርቱ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘዉ የለሚ ኢንደስትሪያል ፓርክ የሚመረት ሲሆን ጥራቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡

በፓስፖርቱ ገፆች ላይ የሀገር ገፅታ የሚያስተዋዉቁ የኢትዮጵያ መለያዎች እንደተካተቱበትም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review