የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ጋር ተወያዩ

AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ካጃ ካላስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ካለው የቡድን 20 የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣን ጋር አመርቂ ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እንዲሁም ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በውይይቱ ዶክተር ጌዲዮን፣ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኮሚሽን ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review