AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት መንግስታት ጋር ያላቸው ትብብር ተምሳሌታዊ መሆኑን እና ይህ የተጠናከረ ትብብር የአመራሩ ቁርጠኝነት ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጊልስ ሚቻውድ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጊልስ ሚቻውድን በቢሮአቸዉ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራሉ በውይይታቸው፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸው ተልዕኮዎች እንዲሳኩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኘ እና በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጊልስ ሚቻውድ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት መንግስታት ጋር ያላቸው ትብብር ተምሳሌታዊ መሆኑን አንስተው፣ ይህ የተጠናከረ ትብብር የአመራሩ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስምሪትንም ለማስፋት ለቀረበላቸው ጥያቄ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።