ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአርባምንጭ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአርባምንጭ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎቹ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት፣ የኮሪደር ልማት እና የአርባምንጭ ስታዲየም የስራ ሂደትን ተመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፣ በሀገሪቱ ባሉ የተለያዩ የክልል ከተሞች እየተሠራ ያለው ልማት የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የህዝብ ተሳትፎ ያረጋገጡ መሆናቸው መልካም ተሞክሮ መሆኑን ገልፀዋል።

በኮሪደር ልማት ስራው ተስፋ ሰጪ ለውጥ ማየታቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ፣ በዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ አዲስ አበባ ተሞክሮዋን ለክልል ከተሞች ማካፈሏን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በነገው እለት በአርባምንጭ ከተማ የሚካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ እንደሚመሩ ይጠበቃል።

+2

All reactions:

116Masresha Demissie Eshete, Us Man Mohammed and 114 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review