AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ፣ በኮሪደር ልማት በተሠራ አስፓልት ላይ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በማቆሸሹ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን 300 ሺህ ብር መቀጣቱን ገልጿል።

ድርጅቱ ከዚህ በፊት 100 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን፣ ድጋሚ ተመሳሳይ ጥፋት በመፈጸሙ የቅጣቱ እጥፍ 200 ሺህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተቀጥቷል።
የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት ስራዋች አዲስ አበባን ውብ ጽዱ በማድረግ የከተማዉ ህዝብ እንዲጠቀምበት፣ የቱሪስት መስህብ እና ከተማው ሌሎች በዓለማችን የሚገኙ ከተሞች የደረሱበትን ዕድገት ደረጃ ለማድረስ ሌት ተቀን 7/24 እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡
ልማት ወዳዱ የከተማዋ ነዋሪም አጥፊዎችን መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።