AMN – የካቲት 18/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ እና የቻይናዋ ጂያንሱ ግዛት ኢኮኖሚ እና ንግድ ኮንፈረንስ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተጀምሯል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመካከለኛው ምሥራቅ ፣ እስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ንጉሥ ከበደ የጂያንሱ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ሽግግር ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ገልጸዋል።
አሞባሳደር ንጉሥ ስትራቴጂክ በሆኑ የኢኮኖሚ መስኮች ኢትዮጵያ ከ ከቻይናዋ ግዛት ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሾነር ዝናቡ ይርጋ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች በመሆኗ የጂያንሱ ባለሃብቶች እድሉን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ፣ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግ ኤምባሲው እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የጂያንሱ ግዛት የንግድ ዳይሬክተር ጄነራል ሲ ዮንግ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተመለከቱት የልማት ሥራዎች መደነቃቸውን ገልፀው ፥የጂያንሱ ግዛት ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር እንዲጎለብት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናገረዋል።
በኮንፈረንሱ በጠቅላላው ከ300 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን 140ዎቹ ከጂያንሱ ግዛት የመጡ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።