በኬንያ ህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር፣ ኮንትሮባንድ እና አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ ተሳታፊ በሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ እርምጃ ተወሰደ

You are currently viewing በኬንያ ህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር፣ ኮንትሮባንድ እና አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ ተሳታፊ በሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ እርምጃ ተወሰደ

AMN – የካቲት 19/2017 ዓ.ም

በኬንያ ህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር፣ ኮንትሮባንድ እና አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ ተሳታፊ በሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ እርምጃ መውሰዱን የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል አስታውቋል፡፡

የኬንያ ፀጥታ ኃይል የወሰደው የማጥራት ዘመቻ ስኬታማ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በማርሳቤት እና ኢሲኦሎ ካውንቲ የመሸገው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መበታተኑ ተገልጿል፡፡

ቡድኑ ዓለም አቀፍ የወንጀል ባህሪ የተላበሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የቡድኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴም ለኬንያ ብሔራዊ የደህንነት ሥጋት እየሆነ መምጣቱን የኬንያ ፀጥታ ኃይል አስታውቋል፡፡

የቡድኑ ዋና መሪ ገመቹ አቦዬ፣ ሌሊሳ በሚል ቅጽል ስሙ የሚጠራው ምክትሉ ሁሴን ጉፉ ሶራ እንዲሁም ቡልቻ የተባሉት ህገ ወጥ ቡድኑን የሚመሩ አመራሮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የኬኒያ ፀጥታ ሀይል “ኦፕሬሽን ኦንዶአ ጃንጊሊ” ብሎ በጠራው ዘመቻው በቡድኑ የአደንዛዥ ዕፅ እና የፕሮፓጋንዳ ማዕከል ላይ በወሰደው መጠነ ሰፊ ዘመቻ ማዕከላቱን ከጥቅም ውጪ ማድረጉን እና ኔትወርኩንም መበጣጠሱን አስታውቋል፡፡

ህገ ወጥ ቡድኑ ሀሰተኛ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር ለማተም የሚጠቀምባቸውን ማሽኖች እና የጦር መሣሪያዎችን የፀጥታ ኃይሉ በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

በቀጣይም አካባቢውን የማረጋጋት፣ ዘላቂ ሠላም የማስፈን እና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ የኬቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review