የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በህብረት ሲቆሙ ሁሉን አቀፍ ድል መቀዳጀት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ታላቅ ድል ነው – የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ

You are currently viewing የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በህብረት ሲቆሙ ሁሉን አቀፍ ድል መቀዳጀት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ታላቅ ድል ነው – የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ

AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በህብረት ሲቆሙ ሁሉን አቀፍ ድል መቀዳጀት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ታላቅ ድል መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ።

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ የፊታችን የካቲት 23 ቀን 2017 ይከበራል።

ድሉን በማስመልከት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እንደገለጹት የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በሀገር ፍቅር፣ በዓላማ ፅናት፣ በመንፈስ ጥንካሬ፣ የአልሸነፍ ባይነት ወኔ እና አንድነታቸውን ያሳዩበት ነው።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ በአብሮነትና በወንድማማችነት መንፈስ ጠላትን ድል ያደረጉበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በዚህም የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በህብረት ሲቆሙ ድል መቀዳጀት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ብሎም አቅምና የሞራል ልዕልና እንዳለን ያሳየንበት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የመጣውን ጠላት ድል ማድረግ የቻሉት በጋራ በመቆማቸው በመሆኑ ይህም አብረን ከተነሳን የማንሻገረው ችግር እንደሌለ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህን የአሸናፊነት መንፈስ የቀድሞውን በመዘከር ብቻ ሳይሆን ነገን በኢኮኖሚ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በመረባረብ ጭምር መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በዓድዋ ጀግኖች የተገኘውን ድል በመሰነቅ አሁን በኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዘርፍ ተግቶ በመሥራት የኢኮኖሚ ነፃነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን ከዓድዋ ጀግኖች መተባበርንና መደማመጥን እንዲሁም የሀገር ፍቅርን በመውረስ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በአሸናፊነት የመወጣት ልምድን ልንማር እና ልናዳብር እንደሚገባ መጠቆማቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

May be an image of 1 person

All reactions:

4141

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review