የዓድዋ ድል ሀገር እና ነጻነት ከጊዜያዊ ልዩነቶች እንደሚበልጡ ትምህርት የሚሰጥ ነው-ዶክተር ተሾመ አበራ

You are currently viewing የዓድዋ ድል ሀገር እና ነጻነት ከጊዜያዊ ልዩነቶች እንደሚበልጡ ትምህርት የሚሰጥ ነው-ዶክተር ተሾመ አበራ

AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የዓድዋ ድል ሀገር እና ነጻነት ከጊዜያዊ ልዩነቶች እንደሚበልጡ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የማህበራዊ ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር ተሾመ አበራ ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር ተሾመ አበራ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ፣ የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ በአለም የታሪክ መዝገብ ውስጥ የተጻፈበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚያን ዘመን ከፍተኛ የፖለቲካ ልዩነቶች እና ጥያቄዎች እንደነበሩ በማንሳት ኢትዮጵያዊያን በሀገር ጉዳይ ሁሉም በአብሮነት መሰለፋቸውን እና በጀግንነት መዋደቃቸውን አስታውሰዋል፡፡

ቴክኖሎጂን ያልታጠቁ በቂ የመገናኛ አቅርቦት ያልነበራቸው ነገር ግን ለሀገር ክብር በጋራ መትመም ያልተቸገሩት ኢትዮጵዊያኑ በራሳችው የመገናኛ መንገድ በብርቱ ክንዶቻቸው ጠላትን አሳፍረው መልሰዋል ያሉት ምሁሩ ይህ ሳይነጋገሩ የመግባባት እና ሀገር በቀል እሳቤ ሁነቶችን በተግባር መግለጥ የአሸናፊነታቸው ሚስጥር ነው ብለዋል፡፡

ዓድዋ ለአሁኑ ትውልድ አብሮነትን የሚያስተምር ለሀገር ክብር እና ሉዐላዊነት በጋራ መቆምን በውል የሚያስገነዝብ ነው ያሉት ዶክተር ተሾመ የአሁኑ ትውልድ ታሪኩን በውል መገንዘብ እና አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበትም ምክረ ሃሳብን ሰንዝረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review