AMN – የካቲት 21/2017 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ባህሎቻችን የወል ትርክት አምባ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚከናወነውን 16ኛውን የባህል ፌስቲቫል ሳምንት አስጀምረዋል፡፡
ከንቲባዋ መርሀግብሩን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ “ባህሎቻችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው ለሀገር ግንባታ፣ ለህዝቦች መቀራረብ፣ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ለሰላም እና ለወል ትርክት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ” ብለዋል።
“መላው የከተማችን ነዋሪዎች የሚያጋምዱን እና ከሌላው የዓለም ክፍል የሚለዩን ባህሎቻችን ሃብቶቻችን መሆናቸውን በመረዳት፣ የተዘጋጀውን የባህል ፌስቲቫል በጊዮን ሆቴል በመገኘት እንድትጎበኙ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።