ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተለምዶ ኬሻ በጠረባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተለምዶ ኬሻ በጠረባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

AMN – የካቲት 21/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተለምዶ ኬሻ በጠረባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል::

የእሳት አደጋው ሌሊት የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሃመድ በአካባቢ ያሉ ቤቶች የተገነቡበት ግብአት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ እንዲሁም አካባቢው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱ ተደማምሮ የእሳት አደጋው እንዲሰፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ኮማንደር አህመድ መሃመድ ጨምረው አደጋውን ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች በፍጥነት ደርሰው ሰፊ ርብርብ ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው አካባቢው መኪና የማያስገባ በመሆኑ እና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች በመኖራቸው ምክንያት የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም ጨምረው መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review