-በሙዚየሙ ከጣሊያን አገር እንዲመለስ የተደረገው እ.አ.አ በ1935 ኢትዮጵያውያን ከጀርመን ኢንጂነሮች ጋር በመተባበር የሰሩት የመጀመሪያ የኢትዮጵያ አውሮፕላንን ጨምሮ ሌሎችም ታሪካዊ ቅርሶች ይገኛሉ
-በታሪካዊው ሙዚየም የዓድዋ ጦርነትን ያስተባበሩት አፄ ምኒሊክ ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡልን እና 12ቱ የጦር መሪዎች የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞላቸዋል
-የዓድዋ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምር ውጤት መሆኑን የሚገልፁ 4 የመግቢያ በሮች አሉት
-መታሰቢያው ከምድር በታች ያሉ ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች አሉት
– ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያዎችን ጨምሮ በርካታ አዳራሾችና መዝናኛ ስፍራዎችንም በውስጡ ይዟል
AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም