የዓድዋ ድል ለትውልዱ ጀግንነትን፤ አብሮነትንና አንድነትን ያሥተማረ የጥቁር ህዝቦች የድል በዓል ነው-የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

You are currently viewing የዓድዋ ድል ለትውልዱ ጀግንነትን፤ አብሮነትንና አንድነትን ያሥተማረ የጥቁር ህዝቦች የድል በዓል ነው-የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

AMN – የካቲት 23/2017 ዓ.ም

የዓድዋ ድል ለትውልዱ ጀግንነትን፤ አብሮነትን፤ ማሸነፍን ፤ነፃነትን እንዲሁም አንድነትን ያሥተማረ የጥቁር ህዝቦች የድል በዓል መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልዕክቱም የዓድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያዊያን የጀግንነት ታሪክ የሚዘከርበት አያቶቻችን ዘመን ባልዘመነበት በያኔው ዘመን ፋሽስት ኢጣሊያንን በጦር በጎራዴ ታዋግተው ያሸነፉበት የእኛነታችን ማረጋገጫ ነወ ብሏል፡፡

ዓድዋ የአንድነታችን የህብረታችን ማሳያ ነው፣ ጀግኖች አያቶቻችን ወራሪውን ያሸነፉበት ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት መሆኑን የገለፁበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ጀግኖቻችን እየዘከርን ህብረታችንን በሚያጎሉ ነገሮች ላይ በማተኮር ብቻ ሊሆን ይገባልም ነው ያለው በመልዕክቱ።

የዓድዋ ድል ለትውልዱ ጀግንነትን፤ አብሮነትን፤ ማሸነፍን ፤ነፃነትን እንዲሁም አንድነትን ያሥተማረ የጥቁር ህዝቦች የድል በዓል ነው ያለው ሠራዊቱ፤ በመሆኑም ለሀገራችን ሠላም ዘብ እንደቆምነው ሁሉ በልማቱ መስክም አሻራችንን በማሣረፍ እና የልማት ተሳታፊ በመሆን የኢትዮጵያን ዕድገት ማረጋገጥ ይገባናል ብሏል።

የመከላከያ ሚኒስቴር የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በባለቤትነትና በማስተባበር እንዲመራ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከተቋቋመው ሀገራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የዓድዋ ድል በዓልን ከባለ ድርሻ አካላት እና ከመላው ህዝባችን ጋር በመሆን እያከበረ ይገኛል።

ሥለሆነም ከአያቶቻችን ከአባቶቻችን የተረከብናትን ኢትዮጵያ ማንነቷን አሥከብረን ሠላሟን አሥጠብቀን በጀግንነቷ ፀንታ እንድትዘልቅ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆን እና ለሠላም እና ለልማት ዕድገታችን መታተር ይገባናል ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review