አድዋ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነት፣ የአርበኝነት፣ የአትንኩኝ ባይነት፣ እምቢ ለባርነት ተጋድሎ ልዩ ምልክት ነው-አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ

You are currently viewing አድዋ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነት፣ የአርበኝነት፣ የአትንኩኝ ባይነት፣ እምቢ ለባርነት ተጋድሎ ልዩ ምልክት ነው-አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ

AMN – የካቲት 23/2017 ዓ.ም

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አፈጉባኤው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ አድዋ የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዊያንን ልክ የሚያሳይ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው ብለዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያዊያን በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በአንድነት የተዋደቁበት የሀገራችንን ክብር በደምና በአጥንት የህይወት መስዋዕትነት ለትውልድ ያቆዩበት እጅግ ልዪ ታሪክ ነው ሲሉም ገልጸዋል::

የዛሬው ትውልድ ከትናንትናው የአባቶቹ ገድል በመማር ሀገርንና ህዝብን ከሚያዋርድ ድህነት ለመላቀቅና ሀገራችንን ለማበልጸግ አርአያነት ያለው ተግባር መፈፀም አለብን በማለት አፈጉባዔው መልእክት አስተላልፈዋል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review