ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የካራማራ የድል በዓልን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው

You are currently viewing ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የካራማራ የድል በዓልን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው

AMN- የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች እና ፖሊስ ሰራዊት ማህበራት ህብረት ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የካራማራ የድል በዓልን አስመልክቶ በጦር ሀይሎች መኮንኖች ክበብ የፓናል ውይይት እያካሄዱ ይገኛል።

በፓናል ውይይቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የቀድሞ ሰራዊት አባላት፤ ኢትዮጵያ በጊዜው በሶማሊያ የሀይል አሰላለፍና የጦር መሳሪያ ብልጫ ቢወሰድባትም በአንድነትና በወኔ ድል አድርጋለች ብለዋል።

ለሁሉ መሰረት አንድነትና መተሳሰብ መሆኑን የገለፁት የቀድሞ ሰራዊት አባላት፤ በሀገሪቱ ያለውን መለያየትና ግጭት ወደኃላ በመተው በህብረት ወደልማት መጓዝ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በውይይቱ የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች እና ፖሊስ ሰራዊት ማህበራት ህብረት አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review