የአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጠናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ

You are currently viewing የአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጠናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጠናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮችና ከፍተኛ የግድብ ደህንነት ባለሙያዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃ አዱኛ በተመራው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉብኝት፣ የተፋሰሱ ተጋሪ ሀገራት ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተገኙበት፣ እንዲሁም የካናዳ የግድብ ማህበር፣ የአውስትራሊያ የትልልቅ ግድቦች ማህበር እና የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማህበር አመራሮች፤ ከዛምቢያ የዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡

የግድብ ጉብኝቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውና በናይል ተፋሰስ የግድብ ደህንነት ማእከል ለማቋቋም በሚመክረው አለምአቀፍ የምክከር መድረክ አካል መሆኑን ማወቅ መቻሉን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የካቲት 15 የናይል ቀን በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት ግብጽ የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዳይጎበኝ በይፋ ቅስቀሳ ብታካሂድም የተፋሰስ ሀገራት ሚኒስትሮችና ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review