ባርኮድ የተካተተበት ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄያቸውን እስካሁን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በቀሪዎቹ 6 ቀናት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ

You are currently viewing ባርኮድ የተካተተበት ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄያቸውን እስካሁን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በቀሪዎቹ 6 ቀናት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባርኮድ የተካተተበት ደረሰኝ ለማሳተም እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜ ሊጠናቀቅ የቀሩት 6 ቀናት ብቻ መሆኑን ገልጿል፡፡

ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ ባርኮድ የተካተተበት ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄያቸውን በማቅረብ አሳትመው መጠቀም የሚጠበቅባቸው 113 ሺህ 37 የደረጃ “ሀ” ፣ የደረጃ “ለ” እና በፈቃደኛነት ደረሰኝ የሚጠቀሙ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች አሉ ሲልም ገልጿል።

ይሁን እንጂ እስከ አሁን ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ መሆናቸውን አመላክቷል።

ስለሆነም ልዩ መለያ ኮድ የተካተተበትን ደረሰኝ ለማሳተም ሁሉም ግብር ከፋይ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ብቻ ጥያቄውን ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ማስታወቁን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር የክልሎችን እና የሁለቱን የከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ባርኮድ የተካተተበት ደረሰኝ ለማሳተም ግብር ከፋዩ ጥያቄውን የማቅረቢያ ጊዜን በአንድ ወር በማራዘም የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review