AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሰፋፊ የብስክሌት መንገዶች መገንባታቸውን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ብስክሌት እና ስኩተር ማምረት መጀመሩን ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት ሰፋፊ የብስክሌት መንገዶች መገንባታቸውን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ብስክሌትና ስኩተሮችን ማምረት መጀመሩን የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ተናግረዋል።
በኢትዮ – ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና በቻይና ኩባንያ ትብብር የሚመረቱት የኤሌክትሪክ ብስክሌቶች ጥራትና ጥንካሬ እንዲኖራቸው ተደርጐ መመረት መጀመራቸውን አምባሳደር ሱሌይማን አብራርተዋል።
ስኩተሮቹ አንድ ጊዜ ቻርጅ ከተደረጉ በኋላ እስከ 30 ኪሎሜትር መጓዝ ይችላሉም ተብሏል።
በአዲስ አበባ በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ብቻ ከ100 ኪሎሜትር በላይ የብስክሌት መንገድ ተገንብቷል።
ይሄም የኤሌክትሪክ ብስክሌትና ስኩተሮች ተፈላጊነት ከፍ እንዲል አድርጓል የተባለ ሲሆን የትራንስፖርት ችግርን በማቃለል ረገድም የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ተመላክቷል።
ኢትዮ – ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎችን በውስጡ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው፡፡
በካሳሁን አንዱዓለም