239ኛ የማድሪድ ደርቢ በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

You are currently viewing 239ኛ የማድሪድ ደርቢ በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

AMN-የካቲት 26/2017 ዓ.ም

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናቢው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል።

ሪያል ማድሪድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ የ239ኛ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ በሎስ ብላንኳቹ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለሎስ ብላንኮቹ ሮድሪጎ እና ብራሂም ዲያዝ የማሸነፊያ ግቦችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

የአትሌቲኮ ማድሪድን ብቸኛ ግብ ጁሊየን አልቫሬዝ አስቆጥሯል።

አርጀንቲናዊው የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝ በዚህ አመት በሁሉም ውድድሮች ለቡድኑ 22 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል ።

በሌላ ጨዋታ ቦርስያ ዶርትመንድ ከሊል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ ቀጣይ ረቡዕ ዕለት በዋንዳ ሜትሮ ፖሊታኖ ምሽት 5 ሰዓት ሲል ይደረጋል ።

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review