AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም
ባህር ዳር ኅብረተሰቡ በሚዝናናባቸው መናፈሻዎች፣ ብስክሌት በነጻነት ማሽከርከር በሚያስችሉ ሰፋፊ መንገዶች እየተዋበች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ጣናን ከልሎ የነበረው ጢሻ ተገላልጦ የሐይቁ ድብቅ ውበት ፍንትው ብሎ መመልከት ሀሴትን ያጎናፅፋል ብለዋል፡፡

ለአገልግሎት ክፍት የሆኑትም ሆነ በሂደት ላይ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ በዘላቂነት ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግሉ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መንፈስ ሊጠብቃቸው እና ሊንከባከባቸው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡