ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመለከቱ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመለከቱ

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመልክተዋል።

ፋብሪካው በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ወደሥራ የሚገባ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን 3 ሚሊዮን ሄክቶሊትር የማምረት አቅምም አለው ተብሏል።

የአስተዳደር ሥራን ወደ ሕዝብ ለማቅረብ የቀበሌዎች መጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በየአካባቢው ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አስተዳደር ለመፍጠር (power devolution) ጥረት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከዚህ አንጻር በአምቦ ወረዳ የአንድ ቀበሌ እንቅስቃሴ በጉብኝት ወቅት መታየቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በዚህ ቀበሌን የማብቃት ተግባር በክልሉ 7342 ቀበሌዎች መደራጀታቸውን እና 50,000 የሰው ኃይል እንደተመደበላቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በወረዳዎች ተማክለው የነበሩ ሞያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በቀበሌ ደረጃ በተገቢው የሰው ኃይል እየተሰጡ እንደሚገኙም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወንጪ ደንዲ ኤኮ ሎጅ አካል የሆነው የደንዲ ክፍል ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

የሥራው የሲቪል ግንባታ ሥራዎች ምዕራፍ ተጠናቆ አሁን የማጠናቀቂያ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውም ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review