በዩሮፓ ሊግ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከሪያል ሶሲዳድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

You are currently viewing በዩሮፓ ሊግ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከሪያል ሶሲዳድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

AMN-የካቲት 27/2017 ዓ.ም

የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ከ2 ሰዓት ከ45 ጀምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡

የእንግሊዙ ክለብ ወደ ስፔን ተጉዞ በሪል አሬና ስታዲየም ከሪያል ሶሲዳድ ጋር የሚያደርገዉ ጨዋታ ተጠባቂ ነዉ፡፤

ሁለቱ ክለቦች በሊጎቻቸዉ ደካማ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ሲሆን ቀያይ ሴይጣኖች ከኤፍ ኤ ካፕ በፉልሃም በመለያ ምት ተሰናብተዉ እና ባለሜዳዉ ሶሲዳድ በበኩሉ በላሊጋዉ በባርሴሎና 4 ለ 0 ከደረሰበት ሽንፈት ማግስት የሚያድርጉት ጨዋታ ነዉ፡፡

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ባወጣዉ አዲስ ፎርማት መሰረት ማንችስተር ዩናይትድ በ18 ነጥብ 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቀጥታ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ሪያል ሶሲዳድ በበኩሉ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ 13 ነጥብ ሰብስቦ 13ኛ ደረጃን ይዞ ነዉ ለዛሬ ጨዋታ የበቃዉ፡፡

ሃሪ ማጉዌር እና ማኑዌል ኡጋርቴ በኤፍ ኤ ካፕ ላይ መጠነኛ ጉዳት በማስተናገዳቸዉ እና ለጥንቃቄ ሲባል በዛሬዉ ጨዋታ ላይ እንደማይሰለፉ የክለቡ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

በጉዳት እየተቸገረ የሚገኘዉ የአሞሪም ክለብ ቁልፍ ተጫዋቾች አማድ ዲያሎ፣ ኮቢ ማይኖ እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝም ከጉዳት ምክንያት ወደ ሴባስቲያን ያልተጓዙ ተጫዋቾች ናቸው።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሃም ወደ ኔዘርላንድስ አቅንቶ ከኤ ዜድ አልካማር ጋር ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ሲል ይጫወታል፡፡ FCSB ከሊዮን ፤ፊነርባቼ ከ ሬንጀርስ ሌሎች የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸዉ፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ሲል አያክስ ከፍራንክፈት ፤ሮማ ከ አትሌቲክ ቢልባኦ፤ቦዶ ከ ኦሎምፒያኮስ እና ፕልዘን ከላዚዮን የሚያደርጉት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡

ሁሉም ጨዋታዎች ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ45 ጀምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review