AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም
የህዝቦች አንድነት፣ መተባበር እና ባህል እንዲጎለብት ቀዳሚ አጀንዳ አድርጌ እሰራለሁ ሲሉ 72ኛዉ የቦረና ኦሮሞ አባ ገዳ ሆነዉ ከ71ኛዉ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ባሊ (ስልጣን ) የሚረከቡት አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ ገለጹ፡፡
አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ፣ በቀጣይ የስልጣን ዘመናቸዉ ከህዝብና ከመንግስት ጋር በመሆን ሰላምና ልማትን ለማምጣት ጠንክረዉ እንደሚሰሩም ተናገረዋል።
72ኛዉ የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑም ተመላክቷል።
በጫላ በረካ