AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ከተለያዩ የስፖርት ማህበራት የተውጣጡ የአዲስ አበባ የስፖርት ቤተሰቦች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል::
አሰጣልኞች፣ የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ የእግር ኳስ ደጋፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ስፖርት ማህበራት ተወካዮች በዛሬው ዕለት አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
የስፖርት ቤተሰቦቹም፣ ማዕከሉ ሁለንተናዊ ፋይዳ እንዲሰጥ ታስቦ መገንባቱ እጅግ እንዳስደሰታቸው በጉብኝቱ ወቅት መግለፃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::