የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ በስድስት የዓለም ሀገራት ሊያደርግ ነው

You are currently viewing የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ በስድስት የዓለም ሀገራት ሊያደርግ ነው

AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሃላፊ ለማ ያዴቻ አስታውቀዋል፡፡

አየር መንገዱ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8ን አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ ወደ ተለያዩ መዳረሻዎች ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ዋና ሃላፊው፣ ይህም የሴቶችን የመቻል አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ዘንድሮም በስድስት የተለያዩ የዓለም ሀገራት በረራ ለሚያደርጉ ሴት የአየር መንገዱ የበረራ ቡድኖች ሽኝት ተደርጓል::

የንግድ ዘርፍ ዋና ሃላፊው አክለውም አየር መንገዱ የሴቶችን ተሳትፎ በማበረታታት አካታች በሆነ መንገድ በርካታ ሴት አመራሮች እና ባለሙያዎችን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል::

አየር መንገዱ የሴቶችን ተሳትፎ በማስቀጠል ሁሉን አቀፍ እድገት ለማረጋገጥ እየተጋ እንደሚገኝ እና ሴቶችን በመሪነት እና በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍም ውጤታማ ተቋም መሆን እንደቻለ ገልጸዋል፡፡

የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፍዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በኢትዮጵ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው ማርች 8 እንደቀደመው ጊዜ በአዳራሽ ሳይሆን በተለያዩ ተግባራት የሚከበር ስለመሆኑ አመላክተዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሃላፊ ለማ ያዴቻ ፣ የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፍዬ (ዶ/ር)፣ የፕላን እና ልማት ሚንስትር ምፁም አሰፍ (ዶ/ር) እና ሌሎች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review