የከተማዋ ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው- አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing የከተማዋ ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው- አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – የካቲት 30/2017 ዓ.ም

የከተማዋ ወጣቶች ያላቸዉን እምቅ አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ ::

“ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ለ7ተኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየዉ የወጣቶች ዘመናዊ ዳንስ እና ባህላዊ ውዝዋዜ ፌስቲቫል ማጠቃለያ መርሀ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው ፡፡

የከተማዋ ወጣቶች ያላቸዉን እምቅ አቅም እንዲያጎለብቱ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል::

ወጣቶች ነገዓቸውን መወሰን የሚያስችላቸዉን ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሞገስ የስብዕና መገንቢያ ማእከላት ለዚህ ማሳያ ናቸዉ ብለዋል::

ማዕከላቱ ወጣቶች ያላቸዉን ተስጥኦ እንዲያሳዩ ዕድል የፈጠሩ ስለመሆናቸውም ተናግረዋል ::

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ በስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ከሚሰጡ 18 አገልግሎቶች አንዱ ኪነ ጥበብ መሆኑን ገልፀዉ ወጣቶች ያላቸውን ክህሎት እንዲያወጡ እና እርስ በእርስ ልምድ እንዲለዋወጡ አስችሏል ብለዋል::

የወጣቶች ኪነጥበብ ውድድሮች ወጣቶች የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህል እና ወግ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችላቸዉ የገለፁት አቶ በላይ ፌስቲቫሉ አንድነትን እና ህብረ ብሔራዊነትን በማስተሳሰር ወጣቶች ለከተማዋ እድገት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ እንደሚያስችልም ተናግረዋል::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review