AMN-መጋቢት 1/2017 ዓ.ም
የኢትየጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ሁለተኛ ምዕራፍ ሶስተኛ ዙር “ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ ዓውደ-ርዕይ እና የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት እየተካሄደ ነው።
የሁለተኛው ምዕራፍ ሶስተኛው ዙር “ክህሎት ስለኢትዮጵያ” መርሀ-ግብር “ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሀ-ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፀዳለ ተክሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያው ዙር “ስለኢትዮጵያ” መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ ሁለተኛው ዙር ደግሞ በሐረር ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 17 መድረኮች ተዘጋጅተው ስለኢትዮጵያ እንደተመከረበት ተመላክቷል።
በሄለን ጀምበሬ