AMN- መጋቢት 1/2017 ዓ.ም
የሶማሌ እና አፋር ወንድም ህዝብ በጋራ የሚያፈጥሩበት “ኢፍጣር ለአብሮነት እና ለሰላም” ፕሮግራም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በፕሮግራሙ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ እና የአፋር ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፕሮግራሙም በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና አንድነት ለማጎልበት እና ለሀገራዊ ሰላምና ወንድማማችነት ጠቀሜታው የጎላ አበርክቶ አለው።