AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሐም ንጉሤን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ፣ ከአምባሳደሩ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የዲፕሎማሲ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው በኢትዮጵያን እና እስራኤል መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የእስራኤል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያው የተፈጠረውን የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙም ጥሪ ቀርቧል።
የኢትዮጵያ እና እስራኤል ግንኙነት ጥንታዊ እና ታሪካዊ መሠረት ያለው እና በጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የተጋመዱ ናቸው።
በእስራኤል የሚኖሩ ከ180ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላዊያን ለሁለቱ አገራት ግንኙነት ቋሚ የግንኙነት መሠረት መሆናቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡