ባለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የምገባ ስራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የምገባ ስራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ

AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የምገባ ስራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ፣ የምገባ ማዕከሉ ለ834ሺ በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 22 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትም ከ36 ሺህ በላይ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች በቀን አንድ ጊዜ እንዲመገቡ እየተደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

በምገባ ማዕከሉ ከ16 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተገልጿል።

ኤጀንሲው ባለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የምገባ ስራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል ።

ይህንን ስራ ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ኤጀንሲው የምገባ ማዕከሉን የሚመጥን እና ደረጃውን የጠበቀ አዲሱን ሎጎ ይፋ አድርጓል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review