በድሬዳዋ የተገነባ የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር መኖሪያ መንደር ተመረቀ

You are currently viewing በድሬዳዋ የተገነባ የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር መኖሪያ መንደር ተመረቀ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በድሬዳዋ አስተዳደር የተገነባውን የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር መኖሪያ መንደር መርቀው ከፈቱ።

የመኖሪያ መንደሩን የመከላከያ የመሐንዲስ ዋና መምሪያ በባለቤትነት ያስገነባው ሲሆን የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግንባታውን በተቋራጭነት አካሂዷል።

መኖሪያ መንደሩ በውስጡ 41 ብሎኮች ያሉት ሲሆን የመዝናኛ፣ የህክምናና የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።

በኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ የተመራው ከፍተኛ የወታደራዊ መኮንኖች ቡድን ከምረቃው በኋላ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ሌተናል ጀነራል ደስታ አብቼ፣ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተሳታፊ ሆነዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሶስት ቢሊየን ብር በሆነ ወጪ በድሬዳዋ የተገነባው የሰራዊቱ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት፤ የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል እና ከፍተኛ የፌዴራልና የከተማው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይመረቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review