AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፀፀምን ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመልካም አስተዳደር ተወካዮች ጋር ገምግሟል፡፡
በግምገማው የቢሮው አማከሪ አቶ ገብሬ ዳኘው፣ አስቀድመው ከተለዩ ከአስራ አንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል ዘጠኙ መፈታታቸውን ጠቅሰው፣ ያልተፈቱ እና በሂደት ላይ ያሉ አራት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ እና በቅርቡ የሚፈቱ መሆኑን ገልጸዋል።
ስራው በውክልና እየተሰራ ያለ ቢሆንም የመልካም አስተዳደር ስራ ከፍተኛ ስለሆነ በትጋት መሰራት ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
አፈፃፀሙም እስከታች ተወርዶ ስለሚታይ መረጃው በአግባቡ ተደራጅቶ ሊቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አንዳንድ ወረዳዎች የወንጀለኞች መደበቅያ የሆኑ ሥፍራዎች፣ አግልግሎት የማይሰጡ ባሶች፣የፖሊስ ኮሚኒቲ አገልግሎትአለመስጠት፣ የፖሊስ ማዕከል አገልግሎት ጥሪ አለመኖሩ እንደ ችግር ተጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በሃይማኖት ተቋማት፣ የውስጥ ችግሮች እና የድምፅ ብክለት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደነበሩ መጥቀሳቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሌሎች በርከታ ችግሮችም ከተሰብሳቢዎቹ በተነሱ ሃሳቦች ለመረዳት መቻሉ ተመላክቷል፡፡