ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መሥራት የሚያስችሏቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ከኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር የባህል ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር መይሊን ሱዋሬዝ አልቫሬዝ ፈርመውታል።

የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ በዚሁ ወቅት፤ በኢትዮጵያ የተሳካ ቆይታ እንደነበራቸው ተናግረዋል።

በቆይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት የረጅም ዘመናት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በፊርማ ስነስርዓቱ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያና ኩባ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በቀጣይ በባህል፣ በስፖርት፣ በቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን እንደተናገሩ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review