አዲስ አበባ በኮሪደር እና በወንዞች ዳርቻ ልማት በፈጣን ሁኔታ እየተገነባች ነው -አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing አዲስ አበባ በኮሪደር እና በወንዞች ዳርቻ ልማት በፈጣን ሁኔታ እየተገነባች ነው -አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN-መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ በሚዘልቀውና የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት አካል በሆነው ከእንጦጦ ኪዳነምህረት በሐምሌ 19 አድርጎ ቀበና ድረስ የሚገነባው የወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ ለተሰማሩ ሠራተኞች የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት፣ አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ሌት ተቀን በፈጣን ሁኔታ እየተገነባች ነው ብለዋል።

በቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ እየተሳተፉ ያሉ እና የተዘጋጀውን የእራት ማዕድ የተቋደሱት አሰር ኮንስትራክሽን እና ሜልኮን ኮንስትራክሽን የተሰኙ የስራ ተቋራጮች እና መላው ሠራተኞቻቸውም በሳምንት 7 ቀናት በቀን 24 ሰዓት በመስራት የከተማ አስተዳደሩን ውጥኖች ለማሳካት እያሳዩት ላለው ቁርጠኝነትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው፣ በወንዝ ልማት ስራው ላይ እየተሳተፉ ያሉ ሠራተኞችን አመራሩ በቀንም ሆነ በሌሊት ስራቸውን በቅርብ እየደገፈ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የእራት ማብላት መርሃ ግብሩ ዓላማም ሠራተኞቹ ስራቸውን በበለጠ ውጤታማነት እንዲያከናውኑ ሞራል ለመስጠትና የአመራሩ ድጋፍ እንዳልተለያቸው ለማሳየት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከእንጦጦ ተነስቶ እስከ ፒኮክ በሚዘልቀው የወንዝ ዳርቻ ልማት ውስጥ የሚገነቡት ወንዞች አካል የሆነው እና በቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተካተቱት የወንዝ ቀለበቶች መካከል ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት በመነሳት በሐምሌ 19 መናፈሻ አድርጎ ቀበና የሚደርሰው የወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ነው፡፡ ይህም ፕሮጀክት በቀን 24 ሰዓት ግንባታው እየተካሄደ በመሆኑ አፈፃፀሙ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review