ግብር ከፋዮችን በትምህርት ማብቃት በፍቃደኝነት ታክስን የመክፈል ባህልን ለማዳበር መሰረታዊ ምሶሶ ነው- ገቢዎች ሚኒስቴር

You are currently viewing ግብር ከፋዮችን በትምህርት ማብቃት በፍቃደኝነት ታክስን የመክፈል ባህልን ለማዳበር መሰረታዊ ምሶሶ ነው- ገቢዎች ሚኒስቴር

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

ግብር ከፋዮችን በትምህርት ማብቃት በፍቃደኝነት ታክስን የመክፈል ባህልን ለማዳበር መሰረታዊ ምሶሶ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ መስከረም ደበበ ገልጸዋል።

የሶስተኛ ዙር የታክስ ሞጁላር ስልጠና ያጠናቀቁ ግብር ከፋዬች የምርቃ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በዚሁ መርሐ-ግብር ከክልል እና ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተውጣጡ 4ሺ 414 ግብር ከፋዮች የሞጁላር ስልጠና ተከታትለው በመጨረስ ተመርቀዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ መስከረም ደበበ፣ ግብር ከፋዮችን ለዚህ ምርቃት ማብቃት በሀገራችን ያለውን የታክስ ሞራል ለማሳደግ እና የኢኮኖሚ መሰረትን ለማጠናከር ሚኒስቴሩ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እርምጃ ነው ብለዋል።

ግብር ከፋዮችን በትምህርት ማብቃት በፍቃደኝነት ታክስን የመክፈል ባህልን ለማዳበር መሰረታዊ ምሶሶ መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያምናል ሲሉም ገልጸዋል።

ሚንስትር ዴኤታዋ አክለውም የታክስ ትምህርት በግብር ከፋዮች እና በታክስ ባለስልጣኑ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ እና ግልጸኝነትን በማረጋገጥ መተማመንን ለመፍጠር ብሎም ለሀገር ያለንን የጋራ ሀላፊነትን ለማጠናከር ትልቅ እገዛ አለው ብለዋል፡፡

ለተመራቂዎችም ታክስ አክባሪ ህብረተሰብ ያላት፣ በኢኮኖሚ የጠነከረች፣ እራሷን የምትችል ሀገር ለመገንባት በጋራ መስራት አለብን በማለት መልክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review